الضحى
Ad-Duhaa
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibበረፋዱ እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibመጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡
- Sadiq & Sani Habibድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየቲምንማ አትጨቁን፡፡
- Sadiq & Sani Habibለማኝንም አትገላምጥ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡