الشرح

Ash-Sharh

ሱራ 94 · መካ · 8 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 12

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibልብህን ለአንተ አላሰፋንልህምን? (አስፍተንልሃል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሸክምህንም ካንተ አውርደንልሃል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያንን ጀርባህን ያከበደውን (ሸክም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመወሳትህንም ላንተ ከፍ አድርገንልሃል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበጨረስክም ጊዜ ልፋ፡፡ (ቀጥል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደ ጌታህም ብቻ ከጅል፡፡