التين

At-Tin

ሱራ 95 · መካ · 8 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 28

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibበበለስና በዘይት ወይራ እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሲኒን ተራራም፤
  1. Sadiq & Sani Habibበዚህ በጸጥተኛው አገርም (እምላለሁ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም (ከፊሉን) ከዝቅተኞች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ለእነርሱ ተቆራጭ ያልኾነ ምንዳ አልላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibታዲያ ከዚህ በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? (ነው)፡፡