العلق
Al-'Alaq
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibአንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
- Sadiq & Sani Habibያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
- Sadiq & Sani Habibባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibአየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
- Sadiq & Sani Habibወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
- Sadiq & Sani Habibአየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
- Sadiq & Sani Habibአላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
- Sadiq & Sani Habibይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
- Sadiq & Sani Habibሸንጎውንም ይጥራ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡