البينة

Al-Bayyinah

ሱራ 98 · መዲና · 8 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 100

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት ላይ) ተወጋጆች አልነበሩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(አስረጁም) ከአላህ የኾነ መልክተኛ የተጥራሩን መጽሐፎች የሚያነብ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧ ቀጥተኛ የኾኑ ጽሑፎች ያሉባት የኾነችን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች ግልጽ አስረጅ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች ነው፡፡ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ይገቡባቸወል)፡፡ አላህ ከእነርሱ ወደደ፡፡ ከእርሱም ወደዱ፡፡ ይህ ጌታውን ለፈራ ሰው ነው፡፡